ቀን 9

ሰላም ለናንተ ይሁን
ምንም አንኩአን የዓመት በአላቸው መስከረም ፪፩ ቀን ቢሆንም ፫፩፰ቱ ሊቃውንት የሚከበሩት በየወሩ ፱ኛ ቀን ነው::አነዚህ ሊቃውንት በቁስጠንጠኖ ዘመን በኒቅያ የተሰበሰቡ ናቸው ስብሰባቸው የሆነበት ምክንያት በአስክንድርያ ሀገር ቄስ ሁኖ የተሾመው አርዮስ ስቶ ወይም ክዶ የክብር ባለቤት ወልድን ፍጡር ነው በማለቱ ነበር ቆስጠንጢኖስ ሰፊ አዳራሽ ለያንዳንዳቸውም ወንበርን በውስጡ ካዘጋጀ በሁአላ የአርሱን ወንበር ከአነርሱ በታች አደረገ ከአነርሱም ተሳለመ ሰይፉን፣ በትረ መንግስቱን፣ ቀለበቱን ሰጥቶ "አነሆ ሃይማኖቱ አንደአናንተ ካልሆነ ለዩት ''አላቸው አነርሱም ሕግንና ሥርዓትን ሰሩ ክብር ይግባውና ጌታችንም ከመካከላቸው ይቀመጥ ነበር ። ከዚህም በሁአላ አንደ አንድ ልብ መካሪ አንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው የኦርቶዶክስ አማኞች በዓለም ላይ የሚኖሩበትን ከዚህ በሁአላ ወልድ ከአብ ጋር በመለኮት ትክክል አንደሆነ አስረዱ አየተረጎሙ የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩ የተረገመ አርዮስንና ተከታዮቹን አውግዘው ለዩ የሰሯት ያስተማሯት ትምህርትም ይች ናት
"ነአምን በአሐዱ አምላክ አብ አሃዜ ኩሉ ዓለም ወነአምን በአሐዱ ኤግዚአ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ዋህድ ዘህልው ምስሌሁ...........
ዘቦቱ ኩሉ ኮነ ወዘንበሌሁሰ አልቦ ዘኮነ ....................ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመፅአ ይኮንን ህያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማህለቅት ለመንግስቱ"
አንዲህ ብለው የሃይማኖት ፋናን አቁመዋል ።
ዛሬም ከዚህ ትምህርት ውጭ የሆነ የተወገዘ የተረገመ ይሁን አሜን
አኔም ''ኩሉ ዘኢያፈቅሮ ለአግዚአነ ወአምላክነ ወመድሃኒነ እየሱስ  ክርስቶስ ወዘኢየአምን ልደቶ አማርያም አምቅድስት ድንግል በክሌ ታቦተ መንፈስ ቅዱስ  አስከ ምፅዐቱ ሐዳስ በከመ ይቤ ጳውሎስ ውጉዘ ለይኩን ''  አላለሁ

0/Post a Comment/Comments

Previous Post Next Post