Audio and Video

እንዲህ አለ ጴጥሮስ

 የመድሃኒት እናት

እንተ በህሊና እግዚአብሔር ተገብረት

ለምኝ ድንግል ለምኝ

እዘምራለሁ ለእግዚአብሔር በፍፁም ደስታ

 
እዘምራለሁ ለእግዚአብሔር በፍፁም ደስታ
ላዳነኝ አምላክ ላቆመኝ ከሰዎች ተርታ
እዘምራለሁ ለእግዚአብሔር በፍፁም ደስታ
ላዳነኝ አምላክ ላቆመኝ ከሰዎች ተርታ

እንዳለፈ ውሃ መከራዬን ያስረሳኝ እርሱ ነው
በእጆቹ ደግፎ ለምስጋና ያቆመኝ በፀጋው
መጽናናቴ እያልኩ የምጠራው ውለታው ማርኮኝ ነው
ፍቅሩ አስደነቀኝ ምህረቱ ለኔ ያደረገው

አዝ

ሃይል በድካሜ እንዲገለፅ ይህንን አድርገሃል
ወጀቡን ገጽጸህ ማዕበሉን እኔን አድነሃል
በጠላቴ ፊት በዘይቱ ራሴን ቀብቶኛል
ወደቀ ሲሉ ጠላቶቼ ኃይሌን አድሶታል

አዝ

በኃጥያት ብረክስም በምህረቱ እኔን ጎብኝቶኛል
ፈጽሞ እንዳልጠፋ በመዳፉ በእጆቹ ቀርፆኛል
ተስፋ ያረኩት ምንም የለም ጌታ ካንተ በቀር
ወጥመዴን ስበር ሰንሰለቴን የኃጥያቴን ቀንበር

አዝ

በሁሉ ላይ አንተ ጌታ እንደሆንክ አሁን አውቄያለሁ
ኃይልህ በድካሜ ተገለጠ ሁለን አልፌያለሁ
ይሁን ያልከውን በህይወቴ ፈጸምክ በፍቅርህ
ዳግመኛ በእጅህ ተሰራሁኝ በበጎ ፈቃድህ

አዝ

በሁሉ ላይ አንተ ጌታ እንደሆንክ አሁን አውቄያለሁ
ኃይልህ በድካሜ ተገለጠ ሁለን አልፌያለሁ
ይሁን ያልከው በህይወቴ ፈጸምክ በፍቅርህ
ዳግመኛ በእጅህ ተሰራሁኝ በበጎ ፈቃድህ

አዝ

በሁሉ ላይ አንተ ጌታ እንደሆንክ አሁን አውቄያለሁ
ኃይልህ በድካሜ ተገለጠ ሁለን አልፌያለሁ
ይሁን ያልከው በህይወቴ ፈጸምክ በፍቅርህ
ዳግመኛ በእጅህ ተሰራሁኝ በበጎ ፈቃድህ

 

የያሬድ ውብ ዜማ

ድንግል ትንሳኤሽን...በዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ 

ፍቃዴ ይህ ነው የሰውን ነገር ላለናገር


1/Post a Comment/Comments

  1. በተሰጠህ ፀጋ ተጠቀምበት! በብዙ ነገር ወደ ኌላ አትይ!
    በርታ!
    አገልግል!

    ReplyDelete

Post a Comment